Dataset Viewer
Auto-converted to Parquet Duplicate
text
stringlengths
10
500
audio
audioduration (s)
10
60.5
dialect
stringclasses
1 value
speaker_id
stringclasses
43 values
gender
stringclasses
2 values
ቴክኖሎጅ እየሆነ እየተስፋፋ መምጣቱን ውደውታል
gonder
UJUY1C
female
ሰዊች መረጃን በአግባቡ ካላገኙ የሚከተሉት ችግሮች ያጋጥሟቸዋል።እነርሱም፡-የጤና ለምሳሌ በአንድ አካባቢ ወረድሽኝ በሽታ ቢመጣ መረጃውን ካላገኙ በበሽታው ተጠቂ ይሆናሉ፤የስራ እድል ማምለጥ፡-አንድ ሰው ከመረጃ ምንጭ መረጃ ካላገኘ ስራ ሊያልፈው ይችላል፤በስራ ውጤታማ አለመሆን፡-የአንድን ስር አሰራር መረጃ አለማግኘት በስራ ላይ ኪሳራን ያስከትላል፤የስራ ፈተና ላይ መውደቅ፡-ወደ ፈተና ከመግባት በፊት ስለ ፈተናው ኢንፎርሜሽን ካልሰበሰብን ፈተናውን ማለፍ አይቻልም።
gonder
UJUY1C
female
አወ በእኔ ህይወት ዉስጥ በጣም ጉልህ ሚና የተጫወቱ ብዙ ሰዎች አሉ ። ነገርግን ከሁሉም በላይ በእኔ ህይወት ውስጥ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተው አባቴ ነው። አባቴ ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ባለዉ ህይወቴ ሁሌም ከጎኔ ነው። እንድበረታ ፣ ወደፊት እንድራመድ ፣ ችግሮች ቢያጋጥሙኝ እንኳን ተስፋ እንዳልቆርጥ የሚመ ክረኝ አስተማሪየ እሱ ነው ። የሆነ ፈተና እንኳን ሲያገጋጥመኝ ቶሎ ብየ እማሰበው የእሱን ምክር እና ጥንካሬ ነው። ለዚህም በጣም አመሰግነዋለሁ ።
gonder
UJUY1C
female
እኔ ገንዘብ የምቆጥብበት በባንክ አና በእቁብ ነው። በዋናነት ግን በቁብ እጠቀማለሁ። ምክንያቱም እቁብ ለሰው ልጅ ለመለወጥ መሰረታዊና አስፈላጊ ነው። እቁብ ወለድ ስለለው በቀላሉ ገንዘብን ሰብስቦ ለሚፈለግ ነገር ለማዋል ቀዳሚና ትክክለኛ መንገድ ነው። በእቁብ የብዙ ሰወች ስኬት ላይ ለመድረስ ዋነኛ መንገድ ሁኖ እያገለገለ ይገኛል። ስለዚህ እኔ ለሰወች የምመክራቸው ነገር ቢኖር የሚያገኙትን ገንዘብ እቁብ ላይ በመጣል በመሰብሰብ ህይወታቸውን እንዲቀይሩ እመክራለሁ።
gonder
UJUY1C
female
የከተማ አውራ ጎዳናዎች እና ኤርፖርቶች በአካባቢያችንና በከተማችን አሉ:: እኒህም በቂ የሆነ አገልግሎቶች እየሰጡ የነበሩ እና አሁንም ያሉ ናቸው:: መሻሻል ያለበትም የተበላሹ እና የፈረሱ መንገዶች መጠገን ይኖርባቸዋል::
gonder
UJUY1C
female
ትልቅ ቦታ ላይ ደርሸ ለሌሎች አርያ እሆናለሁ በቤት ውስጥ ስራ አግዛለሁ
gonder
UJUY1C
female
በማህበረሱ ውስጥ አሉ
gonder
UJUY1C
female
የማህበረሰባችን ባህላዊ ውዝዋዜ ስልት ጎንደረኛ ነው። ጭፈራው በተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎች እንደ ከበሮ ፣ መሰንቆ ፣ ክራር በመሳሰሉት የሚታጀብ ሲሆን የራሱ የሆነ ስልተ ምት አለው። ጭፈራውን የሚጨፍሩ ተወዛወዦች በጋራ በመሆን ይከውኑታል። በተጨማሪም ተወዛዋዞች የሚያደርጓቸው ባህላዊ ጌጣጌጦች እና አልባሳት ለክዋኔው የተለየ ውበት ይሰጡታል።
gonder
UJUY1C
female
ታማኝ ሚዲያዎች በመከታተል።አዎ እፈትሻለሁ።የተወሠኑ ማስረጃዎች እፈልጋለሁ።በአርቲስቶች ላይ የምንሠማው ነገር ዩቲቭ ቻናል ላይ ውሸት ይሆንና፤ቃለመጠየቅ ሲደረግላቸው ቲቪ ላይ እውነታውን እንሠማዋለን።
gonder
UJUY1C
female
ያለንበትን የጤና ሁኔታ ለማወ፤ቅ እንቅስቃሴን መስራት እና አመጋገብን ማስተካከል
gonder
UJUY1C
female
አዎ አቅዳለሁ :-የሥራ ዝርዝር በቀን ሊሠሩ የሚገቡ ሥራዎችን በቅደምተከተላቸው መሠረት ለመሥራት እቅድ አወጣለሁ።
gonder
UJUY1C
female
በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም የበዓላት ጊዜያት ከሌሎች ጊዜያቶች ለየት ስለሚል ብዙ ዘመድ አዝማድ በስራ እና በቤተሰብ ተራርቆ የቆየ መገናኛ መንገድ ነው። የአመጋገብ ስርዓቱ፣ ጨዋታው ለየት ያደርገዋል።ስለዚህ በዓልን ቤተሰብ ጋር ማሳለፍ ደሰረ የሚል ጊዜና ደስታን ይፈጥራል።
gonder
UJUY1C
female
ቬሎ፣ሱፍ እንዲሁም የተለያዩ ባህላዊ ልብሶች።
gonder
UJUY1C
female
ዳማከሴ ለምች እንጠቀምበታለን አዘገጃጀቱ ቅጠሉን በመቁረጥ ጭምቅ እያደረጉ የሰውነት አካልን መቀባት
gonder
UJUY1C
female
ስራ ያጡ ወጣቶችን ተደራጅተዉ እንዲሰሩ የሚደረግ ስራ ትልቅ ነገር ነዉ ብየ አምናለሁ ልክ እንደ ሴፍቲኔት የደሮ እርባታ ጣዉላ ቤት የህትመት ስራ በማሰማራት ዉጣቱ ላይ ትልቅ ስራ እየተሰራ ነዉ
gonder
UJUY1C
female
ሐኪምን በመደበኛነት መጎብኘት ለምን አስፈለጊ ነው? ሐኪምን አዘውትሮ መጎብኘት፣ ባይታመሙም እንኳ፣ ለጤና እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ለዚህም ዋነኞቹ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው። መደበኛ ምርመራዎች እንደ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ፣ እና አንዳንድ የካንሰር ዓይነቶች ያሉ በሽታዎችን አስቀድሞ ለማወቅ ይረዱኛል። የትኞቹ ክትባቶች እንደሚያስፈልጉኝ እና መቼ መውሰድ እንዳለብኝ ያሳውቁኛል። *የጤና እንክብካቤ ከማግኘትዎ በፊት ጤናማ ሁነው ለመቆየት ምን ማድረግ ይችላሉ?*የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ * ጤናማ እና ሚዛናዊ አመጋገብ ማድረግ: * በቂ እንቅልፍ መተኛት * ጭንቀትን ማስወገድ * ሲጋራ ማጨስን እና አልኮል መጠጣትን ማስወገድ:
gonder
UJUY1C
female
አእምሮ ለማዝናናት ለሰዉነት ጥንካሬ ለመገንባት ተፅእኖዉ ጤናማ ዜጋ ለመፍጠር ሰላም ያለዉ አእምሮ ለመገንባት ይጠቅማል
gonder
UJUY1C
female
የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ምክንያቱም የተወሠነ ማህበረሰብ አጠቃቀሙን ስለማያውቅ እና ጥቅሙን ስላላወቀ ይህን በማሣወቅ ጥሩ ለውጥ አመጣለሁ።ምክንያቱም፦ስራን ለማፍጠን እና ጊዜን ለመቆጠብ ቴክኖሎጂን ለመከተል ነው።
gonder
UJUY1C
female
ቤተሰባችን እርስ በርስ ይረዳዳል። ለአብነትም የማስታውሰው፣"የዮኒቨርሲቲ" በጨረስኩ ሰአት የመረቂያ ወጨን በሙሉ ትንሽ ወንድሜ እንደሸፈነልኝ አስታውሳለሁ።
gonder
UJUY1C
female
አደንዛዥ እፆችን መጠቀም የሰውነትን ክብደት መቀየር ፣ የግል ንፅህናን አለመጠበቅ ፣ ድብርት ፣ ጭንቀት ፣ የስራ ፍላጎት አለመኖር ፣ እራስን መጥላት እንዲሁም በህይወት መኖርን አለመፈለግ ስሜቶችን ያመጣል።እንደ ባህል የሚቆጠር ሳይሆን ነገርግን አካባቢየ ብዙ ሰው ጫት ይቅማል። ጫት መቃም ለጊዜው የስሜት መነቃቃት ቢፈጥርም በረጅም ጊዜ ለእፁ ጥገኛ በማድረግ የዕለት ተግባርን ያለ እፁ መከወንን አስቸጋሪ ያደርገዋል። በተጨማሪም የኢኮኖሚ ውድቀትን ፣ የቤተሰብ መበተን ፣ ስራፍላጎት መቀነስን ያመጣል።
gonder
UJUY1C
female
እስካሁን የለም
gonder
UJUY1C
female
ቴክኖሎጅን በአግባቡ መጠቀም የተማረ ወጣት ማፍራት ማህበረሰቡም እቅድና አላማ እንዲኖረዉ ማድረግ በቴክኖሎጅ መዘመን አለብን
gonder
UJUY1C
female
በማህበረሰባችን ውስጥ አልቧልታ ወሬዎች መብዛት እና ታማኝ ምንጮችን በትክክል ባለማግኘት የተነሳ ብዙ ዋጋዎች ሲያስከፍለን ይስተዋላል እንደ ምሳሌ በሀገራችን ተከስቶ በነበረዉ የኮሮኖ ቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋት ላይ የተለያዩ አመለካከቶች በመኖራቸው እና ሰዉ ስለበሽታው ባህሪ ቀድሞ በትክክል መረጃ ባለማግኘቱ ብዙ ሰዎችን ለሞት ዳርጓል።ስለሆነም ከእንደዚህ አይነት ችግሮች ህብረተሰቡን ለማዳን የተማረው አካል በማስረጃ ተደግፎ ላልተማረው ማህበረሰብ እውነተኛ መረጃዎችን በማቅረብ ችግሮችን ቀድሞ መከላከል ይቻላል።
gonder
UJUY1C
female
ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያነሳሳቸው ነገር ትምህርታዊ ፍቅር፣ የራሳቸውን እምነት፣ አብረኝነት ያለው አካባቢ እና ተነቃቂ አስተማሪ ነው። እነዚህ ከተጠናከሩ፣ ተማሪዎች በመማር ደስ የሚላቸው እና እርምጃ የሚወስዱ ይሆናሉ።
gonder
UJUY1C
female
ሁሉንም ሚዲያዊች ፡-ቲቪ ፤ሬድዬ ፤ቲክቶክ እና ይትዩብ ለመዝናኛ እና ለዜና ምንጭነት እጠቀማለሁ።ነገር ግን ከእውነተኛነት እና ከታማኝነት አንፃር ቲቪን እና ሬድዬን እመርጣለሁ ምክንያቱም እሚሰራጨው ዜና ወይም ኢንፎርሜሽን ተጠያቂነትን ስለእሚያስከትል።ፈጣን ፤አዲስ መረጃ ከማድረስ፤ከአቀራረብ አኮያ ቲክቶክ፤ዩትዩብ እመርጣለሁ።ነገር ግን ትክትክ እና ይትዩብ ብዙውን ጊዜ ታማኝ አይደሉም።ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ የተጠያቂነት መስፈርት ስለሌላቸው።
gonder
UJUY1C
female
በእኛ ቤት ውስጥ ከበፊት ጀምሮ እንደ ምግብ ማብሰል እና ጽዳት የመሳሰሉ የቤት ስራወች በአብዛኛው የምንሰራው ሴቶች ነን።አሁን አሁን ግን በትንሹም ቢሆን ወንድሞቸ በቤት ውስጥ ስራዎች እኛን ማገዝ ጀምረዋል። በተለምዶ እኔ ምግብ የመስራት ሀላፊነት ያለኝ ሲሆን ታላቅ እህቴ ደግሞ ታናናሽ እህቶቻችንን የመንከባከብና የማስጠናት ስራ ትሰራለች። ወንድሞቸ ደግሞ በፅዳት ያግዛሉ። ይህ ሀላፊነት የሚወሰነው በእርስ በርስ ስምምነት ነው። ነገር ግን ይህ በአብዛኛው የሚሆነው ነው እንጅ እንዳስፈላጊነቱ የምንወስደው ሀላፊነት ሊቀያየር ይችላል።
gonder
UJUY1C
female
እንደየ ሰርጉ ሁኔታ ዘመናዊ ከሆነ በቬሎ፣በሱፍ በባህላዊ ከሆነ ደግሞ ነጭ ጥበብ ቀሚስ፣ጃኖ፣ካባ ይለበሳሉ።
gonder
UJUY1C
female
ቤተስቦቼ እርስ በርስ አሚደጋገፋት በቤት ሰራ፣በገንዘብ፣እኛን በመንከባከብ እና በማስጠናት። በቤት ስራ ስንል፦እናቴ እንጀራ እምትጋግር ከሆነ አባቴ ምግብ ሊሰራ፣ቤት ሊያፀዳ ይችላል። በገንዘብ፦ወጪን መጋራት ልንለው እንችላለን።ከነዚህም መካከል ለቤት አስቤዛ፣ለእኛ የትምህርት ቤት ክፍያ፣ለልብስ እንዲሁም ለሌሎች አሰፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ወጪን ይጋራሉ። እኛን በመንከባከብ እና በማስጠናት፦ንፅህናችንን በማስጠበቅ፣የቤት ስራ በማሰራት እና በመሳሰሉት ነገሮች ይደጋገፋሉ።
gonder
UJUY1C
female
ባህርዳር ከተማ የጣና ሀይቅና ገዳማት ለመጎብኘት እና ለመዝናናት ምቹ ነበር
gonder
UJUY1C
female
ለምሳሌ ያህል በጉልበቴ፣በሀሳብ ካለ በገንዘብ
gonder
UJUY1C
female
አወ።የሚያፈስ ቤቶችን በመጠገን፣ አልባሳት በመሰብሰብ፣እንዲሁም ሲታመሙ ሳንቲም ሰብስቦ በማሳከም እርዳታ አደርጋለሁ።
gonder
UJUY1C
female
አገልግሎቱን ገካገኘሁ በዃላ በግልጽ ስለአደረክልኝ አመሰግናለሁ ብየ በመንገር
gonder
UJUY1C
female
- የመግባባት ፍላጎታቸው ይጨምራል:: - የማወቅ ጉጉታቸው ያድጋል:: - ነገሮችን የመገንዘብ እና የመመርመር አቅማቸው ከፍ ይላል:: - ፀባያቸው እየተስተካከለ እና ስነ ስርአታቸው ይጨምራል::
gonder
UJUY1C
female
እንክብካቤና ድጋፍ። ብሬን፣ ኬን፣ውልቸር፣ ክራች፣ የምልክት አስተማሪ ወዘተ።
gonder
UJUY1C
female
ትራንስፖርት ትልቅ ውጭ ያስዎጣል:: በሳምንይ እስከ 700 ብር ወጭ አደርጋለሁ:: ወጭንም ለመቀነስ የምወስደው የተሻለው መፍትሄ ወክ እያደረጉ በእግር መሄድ ጥሩ ነው:: ምክንያቱም እንቅስቃሴ ለጤናም ወሳኝ ስለሆነ::
gonder
UJUY1C
female
የእንግሊዘኛ ትምህርት እወደዋለሁ ምክኒያቱም ብዙነገሮችን ማወቅ ስለምፈልግ
gonder
UJUY1C
female
በመጀመሪያ እኛ ለነርሱ አርአያ ሁነን መገኘት እና በሐይማኖት ተቋም ትምህርት እንዲያገኙ ማድረግ
gonder
UJUY1C
female
በመደማመጥ እና በተረጋጋ መንፈስ በማውራት
gonder
UJUY1C
female
በ ገንዘብ ድጋፍ እና በ ስነልቦና ከገጎናቸው በመሆን
gonder
UJUY1C
female
እሩጫ፣ፑሽአፕ፣በቀስታ ሰውነትን በተለያየ አቅጣጫ ማንቀሳቀስ ወዘተ....
gonder
UJUY1C
female
እደተነሳሁ እዳሪ እወጣና ግብረ ውሀ እወስዳለሁ ከዛም አማን አውለኝ ብየ ወደ ሰራ
gonder
UJUY1C
female
የግል ንፅህና የቤት አያያዝ ንፅህና ሳአት አጠቃቀም
gonder
UJUY1C
female
የትምህርት ጉዞየ በጣም ደስ የሚል ጊዜ ነበር አንደኛ ደረጃ ትምህርቴን የተማርኩት አፄ በካፋ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን በጣም ደስ የሚል ጊዜ ነበር በጣም ብዙ የልጅነት ጊዜ ያሳለፍኩበት ነበር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን የተማርኩት ደሞ ፋሲለደስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን በአካልም በአስተሳሰብም ያደኩበት ጊዜ ነበር አዳዲስ ጓደኞችን ያገኘሁበት ጊዜ ነበር በትምህርቴም መካከለኛ የሚባል ጀረጃ ላይ ነበርኩ ፋሲለደስ የተማርኩት ዘጠኝ እና አስርን ነበር አሰረኛ ክፍል ላይ ዉጤት ስላልመጣልኝ ኮሌጅ ነበር የገባሁት ኮሌጅ ገብቸም በአዋላጅ ነርሲንግ ዲፕሎማ አለኝ
gonder
0G2FAS
female
በህይወቴ ዉስጥ ያጋጠመኝ ተሞክሮ በዓለም ላይ ባለኝ አመለካከት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል ምክንያቱም እኔ በፊት ላይ ሳስብ የነበረዉ ነገር ተምሬ ተመርቄ ጥሩ ስራ ኖሮኝ ራሴንም ሆነ ቤተሰቦቸን ሲቀጥልም ማህበረሰቤን እጠቅማለዉ የሚል አስተሳሰብ ነበረኝ አሁን ላይ ግን እንደዛ አሎነም ምክንያቱም ስራ አላገኘዉም ማህበረሰቤንም ቤተሰቦቸንም እጠቅማለዉ ያልኩት ሰዉ እኔ እራሴ ጥገኛ ሁኛለዉ አስተሳሰቤን ወይም የዕለት ተዕለት ተግባሬን የለወጠዉ ነገር ደግሞ በዚህ ስልጠና መሳተፌ ነዉ ምክንያቱም ይሄን ስልጠና ስወስድ በማህበራዊ ሚድያ እንዴት መስራት እንዳለብኝ አዉቄያለዉ ከዚህ በኅላ ስልኬን በመጠቀም እንዴት መስራት እንዳለብኝ በዚህ ስልጠና ተምሬያለዉ
gonder
0G2FAS
female
ገንዘብ ተበድሬ አላዉቅም
gonder
0G2FAS
female
(ከ300 ቁምፊ በላይ) ጤናማ የመዝናኛ ቦታዎች ለግለሰቦችና ማኅበረሰቦች ከአለመግባባት እና የዕለት ተዕለት ውጥረት ለመላቀቅ፣ ደህንነት ባለበት ሁኔታ ውስጥ አእምሮን ለመቀየርና ሰውነትን ለመንቀሳቀስ አስፈላጊ ናቸው። እነዚህ እንቅስቃሴዎች በአእምሮ ጤና ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ አላቸው፤ ውጥረትን እና እከግንነትን ይቀንሳሉ፣ ደስታን ያሳድጋሉ። በግል ደህንነት ረገድ ደግሞ፣ የማህበራዊ ግንኙነትን አጠናክረው የማንነት ስሜትን ያበረታታሉ። ይህ ሁሉ የሚመራው ወደ ጤናማ እና የተሻለ የስራ አፈጻጸም (ምርታማነት) ነው። በጠቅላላው፣ ጤናማ መዝናኛ ለግሉ እና ለማህበረሰቡ የጤናማ ኑሮ መሠረት ነው።
gonder
0G2FAS
female
ችግር ሲያግጥመኝ የመጀመሪያ እረምጃ የአድረጌ እምወስደው የችግሩን መንስሄ በደንብ ለማወቅ እሞክራለሁ ከዛ እንዳስፈላጊነቱ ለቤተሰቦቸ አማክራለሁ።
gonder
0G2FAS
female
አሉ ለምሳሌ ፊዚክስ አብልጨ የምድበት ምክንያት ቁጥር ካልኩሌት ማድረግ እወዳለሁ
gonder
0G2FAS
female
ግለሰቦችና ማህበረሰቦች ጤናማ የመዝናኛ ቦታዎችን የሚያስፈልጋቸው ምክንያቶች:-እራሳቸውን ለማዳመጥ፤ከሁከትና ብጥብጥ እራስን ለማዳን፤ለእራሳቸው ደህንነት፤እርስ በርስ ለመግባባት፤ሀሳብን በቀላሉ ለመረዳት።ጤናማ የመዝናኛ ቦታዎችን መምረጥ አዕምሮ እንዳይጨናነቅ፤እራስን ከእርብሻ እና ከጉዳት፤ነገሮችን በቀላሉ ለመወያየት፤ለመረዳዳት እና ለመግባባት።ማህበረሰቦች ከጤናማ የመዝናኛ ቦታዎችን እሚመርጡ ክህነት አዕምሯቸው እየሰፋ ከፍተኛ ውጤታማ እና ምርታማ ይሆናሉ።
gonder
0G2FAS
female
ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ለማግኘት የምንሞክረው በኦላይን ገበያ
gonder
0G2FAS
female
ቤተሰቤ እና በማህበረሰቤ ዘንድ እንግዳ ስንቀበል ትላልቆቻችን ከሆኑ ከወገባችን ጎንበስ ብለን የእንግዶችን ሁለቱንም ጉልበት በመሳም ከዛም ከፍ ብለን የእንሱን ጉንጭ ከእኛ ጉንጭ ጋር በማገናኘት በደንብ ስላምታ እንለዋወጣለን ። ከዛም ምግብ ሲቀረብ በአንድ ተለቅ ባለ ትሪ ላይ አራት አምስት እንጀራ ተደርጎ ከተባረከ በኋላ ትላልቆቹ እስኪጠገቡ ይበላል። በመቀጠል ለህፃናቱ ደጎች ያተረፋትን ሰብሰብ ብለን እንመገባለን።
gonder
0G2FAS
female
ፋና ላምሮት እና ዋሸሁ እንዴ ፋና ላምሮት ያዝናናል ልጆችንም ያስተምራል ለትልቅ ነገር ያዳርሳል እንዲሁም ዋሸሁ እዴ ያዝናናል ያስተምራል ።
gonder
0G2FAS
female
በስድብ እና በዝምታ።አሉ በዝምታ
gonder
0G2FAS
female
ቴክኖሎጅ እየሆነ እየተስፋፋ መምጣቱን ውደውታል
gonder
0G2FAS
female
ገንዘብ ተበድሬ አላዉቅም
gonder
0G2FAS
female
በእኛ ማህበረሰብ አንዲት ሴት ለአቅመ ሄዋን ከደረሰች ትታጫለች የእከሌ ልጅ አለች ተብላ ከዛ ልጃችሁን ለልጃችን ተብሎ ሽምግልና ይላካል ። ከዛ ቤተሰቡ ተነጋግረዉ እኔ ለልጄ ይሄን አቀርባለሁ ይላል የሴቷ ቤተሰብም ያላቸዉን ያቀርባሉ ። ከዛ ዉል ይፃፃፋሉ ከዛ በኋላ ነዉ እሚተዋወቁት (እሚግባቡት) የሰርጉ ቀን ይወሰናል ቀለበቱ ፣ ቀሚሱ ፣ጥላ ፣ ቅያሪ ልብስ ገዝቶ ሰርጉ ነገዉን ሊሆን ዛሬዉን የወንዱ ሚዜ ለሴቷ አንደኛ ሚዜ ያስረክባሉ ። ሙሽሮች እና ሚዜዎች ሰርጉ ከሆነ በኋላ ምላሽ ወደ ሴቷ ቤት በግ ይዘዉ ይሄዳሉ ። ከዛ በ5 ቀኑ ለሙሽሮች ስም ይወጣላቸዋል እነሱም እርስበርሳቸዉ ስም ይወጣጣሉ።
gonder
0G2FAS
female
አዎ እንጀራ በሽሮ
gonder
0G2FAS
female
ከሁለቱ ለመዝናኛ ብዙ ጊዜየምመርጠዉ ቴሌቪዥን ነዉ ምክንያቱም ብዙ ቻናሎች በዉስጡ ስላለዉነዉ ለምሳሌ:-እንደ ሙዚቃ፣ በተለያዩ አለም አቀፍ ቋንቋዎች የሚቀርቡ ፊልሞችን ስለሚያሳይ እና 24 ሰዓት ስለሚሰራ ማለትም የሰአት ገደብ ስለሌለዉ ምርጫየ ነዉ።
gonder
0G2FAS
female
በማህበረሰቡ ውስጥ መስተካከል ያለባቸው ተግዳሮቶች ውስጥ የስራ አጥነት ችግር የኑሮ ውድነት ችግርና በቂ የውሀ አቅርቦት ችግር በጥቂቱ የሚገለፁ ናቸው። የስራ አጥነትን መፍታት የሚቻለው ብዙ የሰው ሀይል መቀበል የሚችሉ ፋብሪካዎችን በመገንባትና ስዎችን በመቅጠር ጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው እንዲሰሩ የገንዘብ ብድርና ድጋፍ በማመቻቸት የስራ አጥነትን መቀነስ ይቻላል። የኑሮ ውድነትን መፍታት የሚቻለው ማህበረሰቡ ከአንድ ስራ በላይ ተጨማሪ ስራ እንዲሰሩና ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ በማድረግ ከውጭ ሀገር ምርቶች ይልቅ የሀገር ውስጥ ምርቶችን በአማራጭነት በመጠቀም የኑሮ ውድነትን መቀነስ ይቻላል። በቂ የውሀ አቅርቦትን መፍታት የሚቻለው የውሀ ማጠራቀሚያዎች በደለል እንዳይሞሉ አስቀድሞ በመከላከልና በማፅዳት ተጨማሪ የውሀ ማጠራቀሚያዎችን በመስራት የውሀ አቅርቦትን ችግር መፍታት ይቻላል።
gonder
0G2FAS
female
ጥሩ የሆነ አገልግሎት አገኛለው
gonder
0G2FAS
female
ጥሩ ነው ትምሀርት ለአንድሀገር ሁለንተናዊ እድት ከፈተኛ አሰተዋጽኦ አለው ስለሆነም ሁሉም የመህበረሰብ ክፍል ግንዛቤ እንዲኖረው እና ልጆቹን በትክክል ወደ ትምህረት ቤት መላክ አለበት መንግስትም አሰፈላጊውን የትምህት ቤት እና የትምህርት ግብዓቶች ማሟለት እና ማህበረሰቡ ጋር እጅ እና ጓንት ሆኖ ተቀናጅተው መስራት አለበት።
gonder
0G2FAS
female
የሙሽራው ቤተሰብ ለሙሽሪት ቤተሰቦች ልጃችሁን ለልጃችን ዳሩልን ብለዉ በሽምገልና ስነስርአት ጠይቀዉ ፍቃዳቸውን ካገኙ በኋላ ድግስ ተደግሶ ሙሽሪትና ሙሽራው በሚዜዎቻቸዉና በቤተሰብ ዘመድ አዝማድ በተደሙበት የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ይፈፀማል
gonder
0G2FAS
female
የትምህርት አስፈላጊነት በግለሰብ ደረጃ በመጀመሪያ ሁሉም ሰው ራስን ችሎ ማንበብና መፃፍ እንዲችል ነገሮችን አንብቦ ለመረዳት ራስን በእውቀት ለማበልፀግ በስራ ላይ ከፍ ያለ ደረጃ ለማግኘት ስለ ነገሮች ትክክለኛነትና ጥልቅ እውቀት እንዲኖር ይጠቅማል። በማህበረሰብ ደረጃ የተማረ ብቁ ዜጋን ለመፍጠር በንግግርና በውይይት የሚያምን ማህበረሰብን ለመፍጠር ይጠቅማል ። የትምህርት አሰጣጥ አሁን ላይ ያለው ለውጥ አብዛኛው ማህበረሰብ የቅድመ መደበኛ ትምህርት የማግኘት እድል መስፋፋትና በቤተ ሙከራ የታገዘ ትምህርት ማግኘት መቻላቸው የመሳሰሉት ናቸው ።
gonder
0G2FAS
female
ገንፎ በድስት ውሀ በማፍላት የተዘጋጀውን ዱቄት የፈላ ውሀ ውስጥ በመጨመር ማማሰል መብሰሉ ከተረጋገጠ ገንፎው እቃ ላይ ተዘርግፎ በተልባ እየለወሱ መብላት። ብዙውን ጊዜ ጠዋት ጠዋት ይበላል።
gonder
0G2FAS
female
በቤተሰባችን ውስጥ፣ ምግብ ማብሰል በአብዛኛው የእናቴ ኃላፊነት ነው። ነገር ግን አልፎ አልፎ እህቶቸ ያግዟል። ጽዳትን በተመለከተ፣ ሁላችንም የምንጠቀምበትን ነገር ቤት ልብስ የመመገቢያ እቃ እናፀዳለን።
gonder
0G2FAS
female
የኛ ማህበረሰብ የእድር አባላት ብዙ ጊዜ ሳምንት በሳምንት ይገናኛሉ ። በነዚህ ግዜያት ዉስጥ መገዛት ያለባቸዉን ነገሮች ይወያያሉ ። ለምሳሌ ፦ ድንኳን ፣ ትልቅ ብረትድስት (ጎላ) ፣ መቀመጫ ወንበር የመሳሰሉትን ነገሮች ተሰብስበዉ እና ተስማምተዉ ለመግዛት ወይም የጎደላቸዉን ነገሮች ለማሟላት ይወያያሉ ። ሌላ ደሞ አባላቱ እሚመራባቸዉን ህግ እና ደንቦች ለማዉጣትም ይሰበሰባሉ ፣ ወርሀዊ ክፍያም ለመክፈል ይሰበሰባሉ እና ኮሚቴዎችን ለመሻር ለመለወጥ ተሰብስበዉ አዲስ እሚመረጥም ሆነ እሚቀየር ከሆነም በእጅ ብልጫ የተለያዩ ኮሚቴዎችን ይመርጣሉ ።
gonder
0G2FAS
female
እንዴት እና በምን ፣ምን አይነት ምግብ በምን አይነት መንገድ መሰራት እንዳለበት ለልጆች በማሳወቅ።
gonder
0G2FAS
female
ቤተስቦቼን የምረዳበት መንገድ አቅም በፈቀደ መጠን እነሱ እርዳታ በሚያስፈልግባቸዉ ሁኔታ ሁሉ አግዛለዉ
gonder
2CVOUK
male
በቤተሰቦቼ ወይም በማህበረሰቡ ቤት ዉስጥ የምንጠቀመዉ መድሃኒት ዳማከሴ ፣ ጊዜዋ ፣ ሀረግሬሳ ፣ ጤናአዳም ፣ አስተናግር እና ማር በቡና እነዚህን ቤታችን ዉስጥ አትክልቱን ተክለን ለመድሃኒትነት እንጠቀማቸዋለን ። ባህላዊ ህክምናዎች የወፍ ፣ ኪንታሮት ፣ ቡግንጂ እና ሌላ የተለያዩ ህክምናዎች አሉ። ጥቅም ላይ እሚዉለዉ ዳማከሴ ፦ ምች ለመታዉ ፣ ጊዜዋ እምትባለዋ ለ 7 በሽታዎች መድሃኒትነት ትጠቅማለች ለምሳሌ ፦ ለተቅማጥ፣ ለትዉኪያ ፣ ለትኩሳት... ፣ አስተናግር ፦ ለጭንቅላት ላይ ፈንገስ እና ጤናአዳም ፦ ለሆድ ህመም...መድሃኒቱ ለብዙ በሽታዎች ጥቅም ላይ ይዉላሉ ።
gonder
2CVOUK
male
ሰዎች ከታላላቃቸው እንዲሁም ከእነሱ ብዙ ልምድ ካላቸው ሰዎች ለመማር ምን ማረግ አለባቸው? የእርሶን ተሞክሮ ይንገሩን? *በሕይወቴ ውስጥ ብዙ ውጣ ውረዶችን ስላሳለፍኩ፣ ችግሮችን እንዴት መፍታት እንዳለብኝ የረዱኝ ብዙ ልምዶች አሉ፤ ከሰዎች ጋር መግባባት፣ ትዕግስት፣ ጽናት፣ ይቅር ባይነት፣ትሁት፣የፍቅር ግንኙነት፣ የሥራ ሥነ ምግባር ፣ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፣ለሥራ ቦታ ክብር በመስጠትና በመሳሰሉት ነገሮች ጠቃሚ ልምዶችን መውሰድ ችያለሁ። በተለይ አንዳንድ ሥራን በጋራ ለመሥራት እና እንዴት ጥረት ማድረግ እንዳለብ ልምድ ወስጃለሁ።
gonder
2CVOUK
male
የጤና ተቋማት ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽነቱ ይሄን ያህል አይደለም ። አንድ ያደረጉት ነገር የመዉጫ ደረጀዉ ለዊልቸር እንዲመች ብቻ ነዉ ያደረጉት ። ብዙ ሊሻሻሉ እሚገባቸዉ ነገሮች አሉ ፤ ለምሳሌ ሊደርሱበት እሚችሉት ወይም እሚመቻቸዉ መፀዳጃ ቤት ለነሱ እንዲመች አድርጎ አልተሰራም ፣ በቂ የዊልቸር አቅርቦት የለም ፣ ግቢዉም እሚመች አይነት አይደለም ኮሮኮንች ነዉ ቢያንስ ሊሾ ወይም አሰፓልት መሆን አለበት ። እና ደሞ ካርድ ክፍሉም ፣ መመርመሪያዉም ፣ መድሀኒት ቤቱም እሩቅ ለእሩቅ ነዉ ወዲያ ወዲህ ያመላልሷቸዋል እና አይመቺም ሁሉም ባንድ ህንፃ ላይ ቢሆን ግን ጥሩ ነበር ።
gonder
2CVOUK
male
በአካባቢያችን ከሚዘወተሩ ባህለዊ ውዝዋዜዎች ውስጥ ታዋቂ የሆነ የጎንደር ጭፈራ ወይም ውዝዋዜ ሲሆን በከተማው እና በገጠሩ የተለያዩ የአዘፋፈን ስልቶች ያሉ ሲሆን ልክ እንደ ድሰቃ;ዋጫ ልቅለቃ;ሳንኪ እና የመሳሰሉት ጭፈራዎች ይዘዎተራሉ በተለይ እነዚህ ጭፈራዎች በጥምቀት ቀን;እና በሰርግ ቀን ይታያሉ።በከተማው አካባቢ ስፒከር (ሞንታርቦ) በመጠቀም ወጣቱ የሚጨፍር ሲሆን ወደገጠሩ ደግሞ ድምፅን በመጠቀም አንዱ ሲያቀነቅን ሌሎች በመቀበል የጭፈራ አይነት ሲሆን እናቶ እና አባቶች ኩታቸውን በማደግደግ የሚጨፍሩት የጭፈራ አይነት ነው።
gonder
2CVOUK
male
ወንዞች ለብዙ ጥቅም ላይ ይውላሉ የመጠጥ ተደራሽነትን ለማግኘት, ለምግብ ማብሰያ , ለቤት ንፅህና , ልብሶችን ለማጠብ, የግል ንፅህናችን ለመጠበቅ, አትክልቶች እና ዛፎችን ለማሳደግ, ለእርሻ ሰብል ለማፍራት ወዘተ ለብዙ ጥቅም ይውላል።ውሀውን የሚበክሉ ዋና ነገሮች ከወንዙ ዳር መፀዳዳት , ሽንት በመሽናት, ቆሻሻዎችን በመጣል,ወንዙ ዳር እንስሳቶች እንዲፀዳዱ በማድረግ ብክለት ይፈጠራል። በማህበረሰቡ ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖ ለጤና መታወክ ለምሳሌ በመጠጥ የሆድ ቁርጠት , ተቅማጥ,ማስመለስ ተፅዕኖች ያሳድርብናል።
gonder
8TZ4HL
female
በአካባቢያችን እንደ ወረርሽኝ ያለ የበሽታ ተፅእኖ ለመቋቋም ከዚህ በፊት የተጠቀምንባቸው የማኅበረሰብ ድጋፍ መንገዶች የ የኛ አካባቢ የኮሬላ በሽታ ተከስቶ ነበር።በዚያ ግዜ ለማህበረሠባችን ድጋፍ ያቀረብንበት ከጤና ተቋማት ዉሃ አጋር በብዛት በመቀበል ቤት ለቤት የማደል ስራ እና የአጠቃቀም ግንዛቤ መፍጠር ስራ ሰርተናል።ከዚያ ተሞክሮ ያገኘሁት በጣም ጠቃሚ ትምህርት የራስን እና የአካቢን ንፅህና መጠበቅ፣የውሃ አጋር አጠቃቀም፣ያልበሰሉ ምግቦችን መጠቀም እደለለብን፣ፍራፍሬዎችን በደንብ ማጠብ እዳለብን።እነዚን ትምህርቶች ተምሬአለሁ።
gonder
8TZ4HL
female
ወላጆቻችን የሚያስታውሱት የታላላቅ ሰዎች (ሽማግሌዎች) ክብርና አሁን ላይ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ በብዙ መልኩ ይለያያል። ሽማግሌዎች የአንድ ማኅበረሰብ የሕግ መወሰኛ፣ የፍርድ ቤትና የሰላም ሚኒስቴር ነበሩ። አንድ ታዳጊ ጥፋት ሲያጠፋ ያየው ሽማግሌ ሁሉ የመቅጣትና የመምከር መብት ነበረው። በአሁን ጊዜ ግን ግጭቶች አሁን በብዛት ወደ ፖሊስና ፍርድ ቤት ይሄዳሉ። የሽማግሌዎች ሚና በሕግና በቢሮክራሲ እየተተካ መጥቷል። አሁን ላይ "የእኔን ልጅ አትነካብኝ" የሚል ስሜት ስለበረታ፣ ታላላቅ ሰዎች በልጆች አስተዳደግ ላይ ያላቸው ጣልቃ ገብነት ቀንሷል። ልናጣው የምንችለው አስፈላጊ እውቀት ሽማግሌዎች በምሳሌያዊ አነጋገሮችና በለሰለሰ ንግግር ትልቅ ጠብን የማብረድ ልዩ ችሎታ አላቸው። ይህ "ቃልን የመጠቀም ጥበብ" በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ካልገባ ሊጠፋ ይችላል።
gonder
8TZ4HL
female
በገንፎ ቢያችን ለህፃናት የተለየ ፍቅር በመኖሩ የተለየ መወደድና እንክብካቤ አለ እናም በመጀመሪያ አመቱ በተለይም እስከ ስድስት ወሩ ድረስ የተለየ እንክብካቤና ፍቅር ይሰጠዋል። ከሚሰጠዉ እንክብካቤወች መካከልም የተመጣጠነ ምግብ ዋነኛዉ እነሱም፦ ወተት፣አጥሚት፣ገንፎ፣ሾርባ አወ የጤና ባለሙያዋች የእናት ጡት ወተት በተጨማሪ ለህጻናት እድገት ወሳኚ ነገሮች ናቸው። በባሕላችንም ለህጻናት እድገት ወሳኚ ነገሮች ናቸው። ምክንያቱም ብዙ ልጆችን ያሳደጉ ሰዋች የሚሰጡት ምክር እና አስተዋጾ ነው።
gonder
8TZ4HL
female
አንድ መምህር ከምንም በላይ ሊኖረዉ የሚገባዉ ባህሪይ ታታሪነት ነዉ። ታታሪነት ለመምህርነት ብቻም ሳይሆን ለአንድ ስራ ሆነ ለሌላ ስራ አስፈላጊ ነዉ ። ለምን ካልን አንድ ስራ በታታሪነት ከሰራን ለሙያዉ ተገዢ በመሆን ሌሎች የመምህር ባህርያትንና መርሆችን እንተገብረለን ማለት ነዉ። መምህራን ተማሪዎቻቸውን የተሻለ ዉጤት እንዲያመጡ ሊያደርጓቸዉ የሚገባቸዉ ዋና ዋና የሆኑት 3 ነገሮች እነዚህ ናቸዉ። 1.ለተማሪዎች አርዕያ መሆን ይጠበቅበታል። 2.ሰአት አክባሪ መሆን ይጠበቅበታል። 3.ስራዉን የሚወድ።
gonder
8TZ4HL
female
ስለ አስፈላጊ የጤና መረጃዎችን ምናገኘው በአካባቢያችን ጤና ጣቤያዎች ስላሉ አንዳንዴ ትምህርቶች እና የተለያዩ ምክሮች ይሰጣሉ በተጨማሪ ሰዎችን ያግዛሉ ድጋፍና እርዳታ ያረጋሉ ከዚህ በተጨማሪ በአከባቢያችን ትልቅ ሆስፒታል ስላለ በአጋጣሚ ወደ ሆስፒታል ሄደን መጠየቅ እና ማማከር እንችላለን ከዜ በተጨማሪ የተሰማን ካለ ህመማችን በመጠየክ ስለህመማችን ህክምና ማግኘት እንችላለን ከዜ ውጭ ምናገኝበት ምክኛት የለም እና መፍትሔ እንዲሰጥ እሻለሁ
gonder
8TZ4HL
female
የትራንስፖርት ችግር አለ ምክንያቱም ባለ ጉዳዮች የእለት ተእለት ጉዳያቸዉን ለማከናወን እና ጉዳያቸዉን ለመፈፀም ፣ተማሪዎች ነገ አገርየሚረከቡበትን የእዉቀት ማዕድ ወደ ሚቋደሱበት የትምህርት ገበታቸዉ ለመድረስ ይፋጠናሉ የማለዳዉ ሩጫ በዚህ ይጀምራል በዚህ መሀል የግል ትራንስፖርት አማራጭ ያላቸዉ ሰዎች የከተማዋን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ እየተጋፈጡ ወደ ሚፈልጉት ቦታ ለመድረስ ሲጥሩ በህዝብ እና በብዙኀን የትራንስፖርት አማራጮች የሚጠቀሙ ነዋሪዎች ሩጫ ግን የተፋጠነ አይሆንላቸዉም ልባቸዉ ወደ ጉዳያቸዉ ቀድሞ ቢደርስም ማልደዉ የጀመሩት ሩጫ በዚህ በትራንስፖርት ምክንያት ካሰቡት ቦታ ባሰቡበት ሰአት ተሎ አይደርሱም ይሄ ችግር ሊቀረፍ ይገባል
gonder
8TZ4HL
female
ትኩስና ንጹህ ውሃን ከሳሙና ጋር በመጠቀም ቁስሉን በደንብ ማጽዳት:: ንጹህ ጨርቅ በመጠቀም በቁስሉ ላይ በቀስታ በመጫን ደም ማቆም እና ማሰር።የኢንፌክሽን መከላከያ ባህሪ አላቸው ተብለው የሚታሰቡ እንደ ጥንጁት፣ ጣዝማ ወይም ሌሎች የአካባቢው እፅዋት ቅጠሎችን አጥቦ በማድቀቅ በቁስሉ ላይ ማድረግ የተለመደ ነው። ቃጠሎው እንደተከሰተ ወዲያውኑ የተቃጠለውን ቦታ በቀዝቃዛ (በበረዶ ያልሆነ) ውሃ ውስጥ መዘፍዘፍ ወይም ቀዝቃዛ ውሃ ማፍሰስ። ይህ የሙቀቱን ተጽዕኖ ይቀንሳል። በጣም ከተለመዱት አንዱ ለቃጠሎ የሚሆን ቅቤ ወይም የበግ ስብ መቀባት ነው። ይህ ድርቀትን ለመከላከል እና ህመምን ለመቀነስ ይረዳል ተብሎ ይታመናል።
gonder
8TZ4HL
female
በማህበረሰቡ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጨዋታ ዳማ ንጉሡ በፈለገው ተቀሳቅሶ እየተዘዋወረ መብላት ይችላል ሌላው ደግሞ ስርቆት በጨዋታው መስረቅ አይቻልም ከጭዋታ ውጭ ይሆናል ገበጣ አልፎ አልፎ እንጫወታለን ተመልሶ መብላት አይቻልም በጭዋታው መጭበርበር እና መስረቅ አይቻልም ከጨዋታው ዉጭም ያረጋል ሠኞ ማክሰኞ በብዛት ህጻናት ይጫወታሉ በዚህ ጨዋታ የተሠማሩትን መስመሮች መርገጥ ከጨዋታ ውጭ ያረጋል በጨዋታው መፈረ እና ተንኮል መስራት እሄም ከጨዋታ ውጭ ያረጋል
gonder
8TZ4HL
female
ወላጆች ልጆቻቸው በስልክ እና በኢንተርኔት ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ እና የሚያዩትን ይዘት ለመቆጣጠር የሚከተሉትን ቴክኖሎጂያዊ እና አስተዳደራዊ መንገዶች ቢጠቀሙ ውጤታማ ይሆናል፦1)ስልኩ ላይ የሚጫኑ መተግበሪያዎችን በመጠቀም ልጆች ምን ማየት እንዳለባቸው መወሰን ይቻላል። 2)የስልክ መጠቀምያ ቦታ: ልጆች ስልክ ወይም ታብሌት ሲጠቀሙ በሳሎን ወይም ሁሉም ሰው በሚያይበት ቦታ እንጂ በመኝታ ክፍል ውስጥ ብቻቸውን እንዳይጠቀሙ መከልከል። ይህ ተገቢ ያልሆነ ነገር እንዳያዩ በራስ ሰር ይቆጣጠራል። 3)የመኝታ ሰዓት: ወደ መኝታ ክፍል ስልክ ይዞ መግባት በጥብቅ መከልከል አለበት። ስልኮች ማታ ማታ ሳሎን ወይም ወላጆች ክፍል ውስጥ ቻርጅ እንዲደረጉ ማድረግ። 4)ከስልክ ነፃ ሰዓታት: ለምሳሌ በምግብ ሰዓት ወይም የቤተሰብ ወሬ በሚወራበት ጊዜ ስልክ መጠቀም እንደማይፈቀድ ህግ ማውጣት።
gonder
8TZ4HL
female
በጉልት ገበያ ማህበረሰቡ የሚያደረገው ነገር የለም ግን ማህበረሰቡ የሚያደርግላቸው ነገር ቢኖር እነሱ ባወጡት የገበያ እስኪል ይገዛል እሄን ጉዳይ የሚመለከተው አካል እንዲያየው የተሻለ ነው ከዛ በዋላ ማህበረሰቡ አስተዋጽኦ የሚያደርገው ከዚህ ማህረሰብ የሚያደርጋቸው ነገሮች አንደኛ በጉልበት አቅም ያለው በገንዘቡም ሆነ በተለያዩ ነገሮች ይረዳል እና ሁላችንም የበኩላችንን ብንረዳዳ ጥሩ ነው የተሻለ የገበያ መረጋጋት ሚመጣው በዛ ነዉ እላለሁ ከዜ በመቀጠል ምናገረው የቦታ የገንዘብ ነገር ሁሉ ሚመቻች ሀይል ያስፈልጋል
gonder
8TZ4HL
female
ብዙዉን ጊዜ ለህፃናት ስም የሚያወጡት አያት ናቸዉ ምክንያቱም አያቶቻችን እኛ ስንወለድ ነገሮች መሰረት አድርገዉ ያወጡልናል ማለትም ከጊዜዉ ከሁኔታዉ እንፃር ለምሳሌ አንዲት ህፃን ስትወለድ ምንም ያልነበራቸዉ ወይም ቸግሯቸዉ የነበሩ ወላጆቿ እሷ ስትወለድ ችግራቸዉ ከተፈቀረፈ ለምሳሌ ያክል የስራ እድል ይዛ ከመጣች እና ጨለማዉ ቤታቸዉ በብርሃን በደስታ ሲሞላ የልጅቱ ስም ብርሃን ብለዉ ያወጡላታል ምክንያቱም እሷን ሲወልዱ በእርሷ ምክንያት ጭንቀታቸዉ ሁሉ ስለጠፍ በነገራችን ላይ ልጅ ሲወለድ በረከት ይዞ ነዉ የሚመጣዉ ለዛ ነዉ ጊዜዎችን ሁኔታዎች መሰረት በማድረግ የህፃናት ስም የሚወጣዉ አንዳንዴ ደግሞ ከመፅሀፍ ቅዱስም ይወጣል
gonder
8TZ4HL
female
የተፈጥሮ እፅዋት መጥፋት ተጽዕኖ የአፈር ለምነት መቀነስ እና የውሃ እጥረ ዛፎች እና ሥሮቻቸው አፈርን ይዘው የሚይዙት በመሆኑ፣ መጥፋታቸው የአፈር መሸርሸርን ያፋጥነዋል። የእንጨት እጥረት፣ አብዛኛው የኢትዮጵያ ቤተሰብ ለምግብ ማብሰያ እና ለማሞቂያ የሚጠቀምባቸው የማገዶ እንጨት እና ከሰል ምንጮች እያለቁ ነው። የግብርና ምርታማነት ይቀንሳል፣ ይህም ቀጥተኛ የኢኮኖሚና የምግብ ዋስትና ችግር ይፈጥራል። በአካባቢው የአየር ንብረት ላይ የሚያስከትለው ለውጥ የሙቀት መጠን መጨመር፣ የዝናብ ስርጭት መዛባት ያስከትላል:: ባህላዊ የሕክምና እፅዋት ተደራሽነት ብዙ ባህላዊ መድኃኒት ዕፅዋት የሚበቅሉት በተፈጥሮአዊ ደኖች ወይም በሰው ያልተነኩ የደን አካባቢዎች ውስጥ ነው። እነዚህ አካባቢዎች ለግብርና፣ ለእንጨት ወይም ለከተማ መስፋፋት ሲጠፉ፣ የእፅዋቱም ዝርያ አብሮ ይጠፋል።
gonder
8TZ4HL
female
አንዲት እናት እርግዝናዋን ካወቀችበት ቀን ጀምሮ በአካባቢዋ በሚገኝ ሆስፒታል በመሄድ የመጀመሪያ ምርመራ በማድረግ በሀኪሞች የሚነገሯትን ምክሮች ተግባራዊ በማድረግ ከአመጋገብ ጀምሮ የተለያዩ ምግቦች ቅጠላ ቅጠሎች ገንቢ ምግቦች በመመገብ ራሷንና ልጇን በመጠበቅ ለምሳሌ በቤት ዉስጥ የምታገኛቸዉን ሰላጣ ወተት እንቁላል ጎመን ስጋ ባቄላ በህክምና የሚሰጣትን የአይረን መድሀኒቶች ተከታትላ በመዉሰድ እስከ መዉለጃዋ እስክትደርስ ድረስ ከባድ እቃዎች ባለማንሳት ራሷን ከነዚህ ነገሮች በመጠበቅ ፈሳሽ ነገሮችን በመዉሰድ መዉለጃዋ እስኪደርስ ድረስ ራሷን መጠበቅ ይገባል
gonder
8TZ4HL
female
በማኅበረሠባችን ባሕል መሠረት ጋብቻ ትልቅ ክብር ወገን የጠበቀ ነው ከሽምግልናው ስነስርዓት ስንጀምር ሁለት ጥንዶች ተዋደው ወይም ተፋቅረው አንተ ወይም አንተ ተሆነኛለህ ወይም አንች ትሆኝኛለሽ ብለው ተጠናንተው ከወሰኑ በዋላ በሰፈሩ የተመረጡ ሽማግሌዎች የመላክ ሂደት ነው ሰርግ ሽማግሌዎች ከሄዱ በዋላ ቤተሰብ ከወሰነ በዋላ አብሮ እዴሆኑ አብረው ከአንድ ቤት ሜኖሩበች ቤተሰብ ጓደኞቼ ወገን ዘመድ ተጠርቶ ተጠራርቶ ባንድ ላይ አብሮ እየጠጣ እየበላ ሙሽራዎችን አየመረቀ እየዘፈነ ሜሸኝበት ስረሀት ነው
gonder
8TZ4HL
female
የዋጋ ግሽበቱ ያሳደራቸው ዋና ዋና ተፅዕኖዎችና የወሰድናቸው እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ቀደም ሲል በብዛት የምንገዛቸውን የቅንጦት የሚመስሉ ምግቦችን (ለምሳሌ፦ ፍራፍሬ፣ ስጋ ወይም የታሸጉ ምግቦች) በመቀነስ፣ ትኩረታችንን እንደ ጥራጥሬና እህል ባሉ መሠረታዊ ነገሮች ላይ ብቻ እንድናደርግ አድርጎናል። የገንዘብ የመግዛት አቅም በየቀኑ እየቀነሰ በመምጣቱ፣ ገንዘብን በባንክ ብቻ አስቀምጦ ማቆየት ትርጉም እያጣ መጥቷል። ስለዚህ ቁጠባችንን ወዲያውኑ ወደ ቁሳቁስ (ለምሳሌ፦ ለግንባታ የሚሆኑ እቃዎች ወይም የማይበላሹ የቤት ውስጥ ፍጆታዎች) በመቀየር የገንዘቡን ዋጋ ለማቆየት እንሞክራለን። "አስፈላጊ" እና "ፍላጎት"ን መለየት፦ አሁን ላይ ማንኛውንም ሳንቲም ከማውጣታችን በፊት "ይህ ነገር አሁን ለህልውናችን የግድ ያስፈልጋል?" የሚለውን ጥያቄ ደጋግመን እንጠይቃለን።
gonder
8TZ4HL
female
የዝናብ ለውጦች የዝናብ ወቅት መዘግየት – ቀድሞ በመደበኛ ጊዜ የሚጀምር ዝናብ አሁን በኋላ ይጀምራል ያልተመጣጠነ ዝናብ – አንዳንድ ዓመታት ብዙ ዝናብ፣ ሌሎች ደግሞ እጥረት አንዳንድ ጊዜ ከፍተኛ ዝናብና ጎርፍ መታየት አጠቃላይ ሙቀት መጨመር – ቀድሞ ቀዝቃዛ የነበሩ ወቅቶች አሁን ሞቃት ሆነዋል ረጅም የሙቀት ጊዜ – ሰዎችና እንስሳት ላይ የሚያደርስ ተፅዕኖ የመዝራትና የመከር ወቅት የመዝራት ወቅት መቀየር – ገበሬዎች ቀድሞ ያውቁትን ወቅት አይተማመኑበትም የምርት መቀነስ – በዝናብ እጥረት ወይም በድንገተኛ ዝናብ አንዳንድ ጊዜ ዘር እንደገና መዝራት
gonder
8TZ4HL
female
አንድ መምህር ስኬታማ ሊባል የሚችለው መሰረታዊ የመምህር ባህርያትን ሲያሟላ ብቻ ነው። ስኬታማ መምህር ግልፅ ግብ አስቀምጦ ይሰራል:ላስቀመጠው አላማ ውጤታማነት ይተጋል,ጥሩ መምህር በረዥም ጊዜ ለሚመጣ ውጤት ተግቶ ይሰራል።ተማሪዎችን በማዳመጥ የሚያስፈልግበትን ምክንያት ይለያል ,ቀና አመለካከት ይዞ ይሰራል,ዋና ግቡ ተማሪዎችን ውጤታማ ማድረግ ነው እያዝናና የማስተማር ልምድ አለው ከተማሪ ወላጆች ጋር በየጊዜው እየተገናኘ መረጃ ይለዋወጣል። ዘዴዎች ብዬ የማስበው 1ኛ, ትምህርትቤቶችን ምቹ በማድረግ ማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት 2ኛ, ቤተመፅሀፍትን ሳምንቱን ሙሉ ክፍት ማድረግ 3ኛ, ፈተና በእቅድ መስጠት።
gonder
8TZ4HL
female
ባለፉት አስርት ዓመታት በአካባቢያችን የአየር ንብረት ላይ ለውጥ የሙቀት መጠን መጨመር (በተለይ በበጋ ወቅት)፣ ያልተጠበቀ ዝናብ (አንዳንዴም ከባድ)፣ እና የመዝራት ወቅት መዛባት ሊሆን ይችላል፤ ይህ ደግሞ የግብርና ሥራን በማስቸገር ድርቅን ወይም የጎርፍ አደጋን ሊያስከትል ይችላል፣ ይህም በአጠቃላይ የአየር ንብረት ለውጥ (Climate Change) ምልክቶች ናቸው. የሚታዩ ለውጦች: የሙቀት መጠን መጨመር: በአጠቃላይ የዓለም ሙቀት ከፍ እያለ ቢሄድም፣ በአካባቢዎም የሙቀት ሞገዶች (Heatwaves) በተደጋጋሚ እና በኃይል ሊከሰቱ ይችላሉ.
gonder
8TZ4HL
female
መሞባይል ስልኮች በልጆች የትምህርት ላይ ወይም ከቤተሰብ አባላት ጋር ባላቸው ግንኙነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል ብየ አስባለሁ። ምክንያቱም ልጆች ሞባይል ስልክ ጋር እረጅም ስዓት የሚያሳልፉ ከሆነ ትምህርሞታቸውን ከመከታተል ይልቅ ጌም በመጫወት የተለያዩ ፊልሞችን በማየት በትምህርታቸው ደካማ እንዲሆኑና በስልካቸው ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። እንዲሁም ከቤተሰብ አባለት ጋር ከማሳለፍ ይልቅ ከስልኮቻቸው ጋር ብቻ በመቆየት ከቤተሰብ አባለት ጋር ግንኙነት እንዳይኖራቸው አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል።
gonder
8TZ4HL
female
ለተማሪ የተሻለ የሚሆነዉ የግል ትምህርት ቤት ነዉ ከመንግስት አንፃር ስናየዉ የተሻለ ነዉ ብየ አስባለሁ ምክንያቱም የግል ትምህርት ቤት ለተማሪዎች ጥብቅ ቁጥጥር ያደርጋሉ በየ ሴምስተሩ ወላጆችን እየሰበሰቡ የተማሪን ዉጤት ያሳዉቃሉ ለተማሪዎችም ፍላጎታቸዉን ያሟላሉ ተማሪዎች ገንዘብ እስከከፈሉ ድረስ አስተማሪዉም ሆነ ርዕሰ መምህሩ ፍላጎታቸዉን ያሟሉላቸዋል አንድ ለአምስት አደራጅተዉ ጥናት እንዲያጠኑ ያደርጓቸዋል በተማሪዎች ላይ ትኩረት ይደረጋል መምህር ሲቀጠር ለተማሪ የሚመቸዉን ነገር ያደርጋል በመንግስት ትምህርት ቤቶች ደግሞ ለተማሪ የሚመቸዉን ነገር ቢያደርጉም ቁጥጥር ላይ ግን ደካማ ናቸዉ አስተማሪዎች ለተማሪ ሲያስተምሩ በደንብ በጥልቀት አያስረዷቸዉም በትንሹ ፍንጭ ሰጥተዉ ያልፏቸዋል ያ ሲሆን ተማሪዉ ጥሩ የሚባል ዉጤት አያመጣም ቁጥጥር ላይ ቸልተኝነት ይበዛል
gonder
8TZ4HL
female
በምኖርበት አካባቢ ጋብቻ በዋናነት በሦስት ይከፈላል:: ከጋብቻ በፊት፣ የሰርግ ዕለት እና ከጋብቻ በኋላ ተብሎ ይከፈላል:: ከዛም የተመረጡ ሶስት ሽማግሌዎች ይላካሉ:: ሽማግሌዎቹ "ልጃችሁን ለልጃችን" ብለው ይጠይቃሉ። ቤተሰብ ወዲያውኑ እሺ አይልም፤ "እንመካከርበት" ብለው ለሁለተኛ ወይም ለሦስተኛ ቀጠሮ ያቆያሉ። እዛም ጥሎሽ ይጣላል:: ከዛም የሰርግ ቀን ተቆርጦ ድግስ ይደገሳል፣ ወገን ዘመድ ይጠራል:: የሰርግ እለት ከሰርጉ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ በሁለቱም ወገን ሰፊ ዳስ ይጣላል። ጎረቤትና ዘመድ ተሰብስቦ ጠላ በመጥመቅና እንጀራ በመጋገር ይረባረባል። ሙሽራው ወደ ሙሽሪት ቤት ጉዞ ያደርጋል:: የሙሽሪት ቤት ተዘግቶ ይቆያል:: አናስገባም ሰርገኛ ይጨፋራል:: ከዛም ሙሽራው ከሚዜዎቹ ጋር አሸንፎ ይገባል:: ይበላል ይጠጣል፣ የሀይማኖት አባት ባለበት የቀለበት ስነ ስሮአት ይሆናል
gonder
8TZ4HL
female
በማህበረሰብችን ውስጥ በቤተሰቦች ወይም በጎረቤቶች መካከል የሚነሱ ከባድ አለመግባባቶችን ለመፍታት (ከመደበኛው የፍርድ ቤት ሥርዓት ውጪ) የምንጠቀምባቸው ባህላዊ ዘዴዎች ውስጥ ሽምግልና አንዱ ነው። ሽምግልና የሀገር ሽመግሌዎች ወይም ቤተ ዘመዶች ከሁለቱም ወገን የሆኑ ሰዎች ተሰባስበው የተጣሉ ሰዎችን በማቀራረብ የተጣሉበትን እንዲናገሩ በማድረግ ጥፋተኛ የተባለን በቅጣት እና ድጋሜ እንዳይፈጠር በማግባባት ማስማማትና በማስታረቅ በሀገር ባህል አለመግባባቶችን ለመፍታት የምንጠቀምበት ባህላዊ ዘዴ ነው።
gonder
8TZ4HL
female
የድህረ ወሊድ እንክብካቤ እቅድ እናቶች እና አራስ ሕፃናት ከተወለዱ በኋላ ባሉት ስድስት ሳምንታት ውስጥ የሚያገኟቸውን የተሟላ የጤና አጠባበቅ አገልግሎቶችን ያጠቃልላል። የዓለም ጤና ድርጅት ሁሉም እናቶች እና አራስ ሕፃናት ቢያንስ አራት የድህረ ወሊድ ምርመራዎችን ማድረግ አለባቸው፡- በ24 ሰዓት ውስጥ፣ በቀን 3 (48-72 ሰአታት)፣ ከ7-14 ቀናት እና ከተወለዱ በኋላ ባሉት 6 ሳምንታት ውስጥ። ይህ ከቀድሞው መመሪያ ሁለት የድህረ ወሊድ ጉብኝቶችን ብቻ የሚጠቁም ጉልህ ለውጥ ያሳያል። የጤና እንክብካቤ ተቋማት ወይም የሰለጠኑ አገልግሎት ሰጭዎች የቤት ለቤት አገልግሎት ይሰጣሉ ።ለህፃኑም 6ወር እስኪሞላው የእናት ጡት ወተትና ካለፈው በኃላ ከእፅዋት አትክልት፣ ፍራፍሬ ሰውነት ገንቢ እና በሽታ ተከላካይ ምግቦችን መመገብ አለብን
gonder
8TZ4HL
female
እኛ አካባቢ ያሉ ሠዎች አካባቢያቸውን የሚጠብቁበት ሁኔታ 1.ሠፈር ላይ ያሉ ቆሻሻዎችን ሠብስቦ በማቃጠል 2.ውሀ አርከፍክፎ በመጥረግ 3.ውሀ ያቋቱ ጉድጓዶችን በማፋሠስ 4.የቆሻሻ ማስረጊያ በማዘጋጀት በነዚህ አይነት መንገድ ንፅህናቸውን ይጠብቃሉ። በቆሻሻ አወጋገድ የማያቸው ዋና ዋና ችግሮች ውስጥ በጥቂቱ 1.የቆሻሻ አይነት አለመለየት ለምሣሌ፦ደረቅ፣ፈሣሽ እና በተጨማሪ ጠርሙስና ሌሎች ቆሻሻዎችን አንድላይ መጣል። 2.ማስረጊያ ተዘጋጅቶ ደረቅና ፈሣሽ ማስረጊያው ላይ መጣል። 3.ቤት ወይም ግቢ አፅድቶ ግቢ ውጭ መንገድ ላይ በመድፋት አካባቢውን መበከል ናቸው። እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ዋናው ነገር ለማህበረሠቡ ግንዛቤ መፍጠር፤ቆሻሻን ቤት ለቤት መረከብ እና ቆሻሻን በስርአት የላስወገደን ሠው መቅጣት።እደዚህ እርምጃዎች መውሠድ አለብን።
gonder
8TZ4HL
female
አዎ ምክንያቱም ለመኖሪያ ተብሎ ቤቶች ሲሰሩ እፅዋቶችን ስለሚቆርጧቸዉ ለህክምና የምንጠቀምባቸው የነበሩ ባህላዊ መድሀኒቶች የሚሰሩበት እፅዋት በቀላሉ አናገኝም የሙቀት መጠንም በዛዉ ልክ የመፈጠር እድሉምሰፊ ነዉ የምንፈልገዉን ባህላዊ ለመድኃኒትነት የሚሆኑ እፅዋቶችን ስለሚፈልሱ ልናጣቸዉ እንችላለን በረሀነት ይስፋፋል ዝናብ በመጣ ጊዜም መሬቱ እየተሸረሸረ ይሄዳል የሙቀት መጠን ከሚባለዉ በላይ እየጨመረ ይመጣል ይህንን ለመከላከል ሁላችንም የየራሳችን ጥረት ማድረግ አለብን ለምሳሌ እፅዋቶችን በቆረጥን ልክ መትከል እና መንከባከብ እንደሚገባ የሁላችንም ሀላፊነት ስለሆነ ይህንን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ማወቅ አለብን ያወቅነዉን ነገር ለሌሎች በማስተማር ግንዛቤ በመፍጠር ግዴታችን መወጣት ይገባል
gonder
8TZ4HL
female
ብዙ አይነት ስፖርት እወዳለሁ ለመጥቀስ ያህል እሩጫ ውድድር ፣ ኳስ ጨዋታ፣ የሰርከስ ትርኢት ፣ቦክስ ውድድር እነዚህን ውድድር በጣም የምወዳቸው ሲሆን በተለይ ደግሞ ኳስ ጨዋታ በጣም ይመቸኛል እኔ የምደግፈው ከአገር ውስጥ ክለቦች ፋሲል ከነማ እና ቡና ክለብ ነው በተለይ ፋሲል ከነማ የአጨዋወት ስልት እና ታክቲኩ ድስ ይላል ከሀገር ውጭ ደግሞ ባርሴሎና ከተጫዋቾቹ ደግሞ ሜሲን አድናቂ ነኝ ምክንያቱም የጨዋታው ጥበብ እና የአጨዋወት ስልቱ በጣም ይወደድለታል እናም በጣም ብዙ ጎሎች በማስገባት ሻንፒሆን በመሆን የተለያዩ ሽልማቶችን ስለ ሚወስድ እወደዋለሁ።
gonder
8TZ4HL
female
አዎ የምናጣው ነገር ማህበረሰቦች ተቻችለው የሚኖሩትን በመጥፎ መንገድ ይመርዛል , ባህላችን ይጠፋል, እሴቶች ይጠፋሉ, ተግባብቶ ተከባብሮ የመኖር ሁኔታዎች እየቀነሰ ይመጣል ግጭቶች ይስፋፋሉ ።የውጭ ሀገራትን የአሁኑ ትውልድ በተለይ የውጭ ሀገር ባህልን በመቀበል የራስን ባህል በመተው ለምሳሌ ከአለባበስ ጀምሮ ከባህላችን ያፈነገጠ ውጭ የሆነ የተለያዩ ባህድ አምልኮቶችን ወይም እምነት በማስፋፋት ትውልድም የውጭ ናፋቂ እንዲሆኑ አስተሳሰባቸው በመቀየር ሀገራቸውን እንዲጠሉ በማድረግ ትልቅ ተፅዕኖ አለው።
gonder
8TZ4HL
female
End of preview. Expand in Data Studio
README.md exists but content is empty.
Downloads last month
73